ፍትህ

Personal Blog

"ጀግና ሰው ማለት ሰውን ታግሎ የሚጥል ሳይሆን ፣ በንዴት ግዜ ራሱን ተቆጣጥሮ የሚያልፍ ነዉ !"

- ረሱል ﷺ

4:22
● ከሩዋንዳው የጅምላ ጭፍጨፋ የተረፈች ● ➤ "ሁሉንም ልጆቼን፣ ባሌን፣ ወላጆቼን፣ የባሌን ወላጆችና መላ ቤተሰቦቻቸውን አጥቻለሁ" ➤ "ባለቤቴ የተገደለ ጊዜ እዚያው በብዙ ወንዶች በተደጋጋሚ ደፍረውኛል" ➤ "ዶማ እንኳ ለማንሣት የሚችል አቅም ስለሌለኝ ካለችኝ ጥሪት ላይ ሰው ቀጥሬ ኩርማን መሬቴን የማሳርሰው" ሊድያ ኡዋምዌዚ ዘንድሮ የ46 ዓመት ዕድሜ ጎልማሳ ናቸው። ሩዋንዳዊት ገበሬ፤ ትዳርም ልጆችም የላቸውም። የሚኖሩት በርዋንዳዪቱ ኛንሙጋሊ ከተማ ነው። ሊድያ የዛሬ ሰላሣ ዓመት አካባቢ ርዋንዳ ውስጥ በተፈፀመው ጎሣ የለየ ጅምላ ጭፍጨፋ ሰባ ሦስት ዘመድ አዝማድ ተገድሎባቸዋል። ባለቤታቸው፣ ልጆቻቸውና ሌሎችም የቤተሰባቸው አባላት ኪጊናና ኛሩቡዬ አነስተኛ ከተሞች መካከል ባለው ቾሆዋ ሃይቅ ውስጥ ተጥለውባቸዋል። ሊድያ ዛሬ የሚኖሩት በምኅፃር “ፋርዥ” ተብሎ በሚጠራው ከጅምላ ጭፍጨፋ የተረፉ ሰዎች ድጋፍ ፈንድ በኢትዮጵያ ምንዛሪ ሂሣብ በወር በሚሰጣቸው 950 ብር ድጎማ እየተረዱ ነው። “ዕድሜና ጤና እንዲሰጠኝና ክፉ ሳይደርስብኝ የግዜርን ሞት እንድሞት ብቻ ነው እንግዲህ የምፈልገው” ብለዋል። "ሁሉንም ልጆቼን፣ ባሌን፣ ወላጆቼን፣ የባሌን ወላጆችና መላ ቤተሰቦቻቸውን አጥቻለሁ። በድሮ ጊዜ ሴት ባሏ ሲሞትባት ቤተሰቧ ወይም ሌሎች ሰዎችም ቢሆኑ ይረዷት፣ ይደግፏት ነበር። እኛ ግን ለዚያ አልታደልንም። በወቅቱ እንዲያ ዓይነት ክፉ ዕጣ የደረሰብኝ እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አስብ ነበር። ቆየት ብሎ ግን እንደ’ኔ ዓይነት ብዙዎች እንዳሉ ተገነዘብኩ። ከሁሉም የበለጠ የጎዳኝ ወንድሞቼንና እህቶቼን፣ ልጆቼንና ባሌን መነጠቄ ነው። " ሊድያ ኡዋምዌዚ ሰሞኑን ከአሜሪካ ድምፅ ጋር አጭር ቃለ-ምልልስ ያድምጡ።
14 days ago